ዘሌዋውያን 23:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምታጭዱበት ጊዜ የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ ስጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ ከሰበሰባችሁት እህል የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ አቅርቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከሩን ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤ |
“የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ የመከር በዓል አክብሩ፤ “ከወይን ተክሎቻችሁና ከፍራፍሬ ዛፎቻችሁ ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ፤
“በየዓመቱ ከምታመርቱት ምርት መጀመሪያ የደረሰውን በኲራት ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግን ወይም የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
የመከር መጀመሪያ የሆነውን ያማረውን በኲራትና ለእኔ የቀረበውን ስጦታ ሁሉ ካህናቱ ይውሰዱ፤ ሕዝቡም ሁልጊዜ እህል ሲፈጩ የዱቄቱን በኲራት ለካህናቱ መባ አድርገው ያበርክቱ፤ እኔም ይህንን ሁሉ የሚያደርጉትን ሕዝብ ቤታቸውን በበረከት እሞላዋለሁ።
እግዚአብሔር ይቀበላችሁ ዘንድ ካህኑ ነዶውን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርባል። ካህኑም እርሱን ማቅረብ ያለበት ከሰንበት ቀጥሎ በሚውለው ቀን ነው።
እያንዳንዱ ቤተሰብ ሁለት እንጀራ በመወዝወዝ ልዩ መባ አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እያንዳንዱ እንጀራ እርሾ ገብቶበት ከሁለት ኪሎ የላመ ዱቄት ጋር ተጋግሮ ስለሚሰበሰበው አዲስ መከር ለእግዚአብሔር የበኲራት መባ ሆኖ ይቅረብ።
ከአንድ ዐይነት ሊጥ የመጀመሪያው ክፍል የተቀደሰ ከሆነ ሊጡ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ እንዲሁም የአንድ ዛፍ ሥሩ የተቀደሰ ከሆነ ቅርንጫፎቹም የተቀደሱ ይሆናሉ።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።
እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር።