በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው።
ዘሌዋውያን 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእህል መባውም የተረፈው ዱቄት የአሮን ዘር ለሆኑት ካህናት ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ የሚቃጠል ቊርባን በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተረፈውም የእህሉ ቍርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ቍርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመሥዋዕቱም የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ከእግዚአብሔር መሥዋዕት የተረፈ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእህሉም ቍርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚሆን የእሳት ቍርባን ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። |
በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው።
ይህንንም ለሰባት ቀን በየዕለቱ አድርግ፤ በዚህም ዐይነት መሠዊያው ፍጹም የተቀደሰ ይሆናል፤ የተቀደሰም ስለ ሆነ፥ ሰውም ሆነ ሌላ ነገር እርሱን ቢነካ በቅድስናው ኀይል ቅሥፈት ይደርስበታል።
የእህሉ መሥዋዕት፥ የኃጢአትና የበደል ስርየት መሥዋዕት ለእነርሱ ምግብ ይሁንላቸው፤ በእስራኤል ምድር ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰውን ማናቸውንም መባ ሁሉ ይቀበሉ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ቦታ ካህናቱ ለኃጢአትና ለበደል ማስተስረያ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውን ሥጋ የሚቀቅሉበትና የእህል መሥዋዕት የሚጋግሩበት ክፍል ነው፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ጒዳት እንዳይደርስ ከተቀደሰው መሥዋዕት ሁሉ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጣም።”
ስቡ ለእግዚአብሔር የምግብ መባ ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ወርቹንና ፍርምባውን ያመጣሉ፤ ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም የተመደበ ድርሻ ይሆናል።”
ጠቦቱንም ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ቅዱስ ስፍራ ያርደዋል፤ ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት የበደል ዕዳ መሥዋዕት ልክ ለኃጢአት ስርየት እንደሚቀርበው መሥዋዕት የካህኑ ድርሻ ሆኖ ስለሚሰጥ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።
ካህኑም በዚህ ዐይነት ስለዚያ ሰው ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል፤ የቀረው ዱቄት የእህል መባ በሚቀርብበት ዐይነት ለካህኑ ይሁን።”
“ለአሮንና ለልጆቹ የምትሰጣቸው የሥርዓት መመሪያ ይህ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ በመሠዊያው ላይ እንዲቈይ ተደርጎ እሳቱ ሲነድ ይደር፤
“ስለ ኃጢአት ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕትና ስለ በደል ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕት መካከል ለሁለቱም የሚሠራ አንድ ዐይነት ሕግ አለ፤ ይኸውም የእንስሳው ሥጋ መሥዋዕቱን ለሚያቀርበው ካህን ምግብ እንዲሆን ይሰጣል፤
ለእኔ ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰ መባ ሁሉ፥ ከእህል ቊርባን፥ ስለ ኃጢአት ስርየትና ስለ በደል ካሣ ከሚቀርበውም መባ ሁሉ፥ በእሳት የማይቃጠለው የመባ ድርሻ የአንተና የልጆችህ ነው።
እርሱንም ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ እጣን እንዲያጥን፥ በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ፥ የእኔ ካህን ይሆን ዘንድ መረጥሁት፤ ለቀድሞ አባትህ ልጆችም የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ሰጠኋቸው።