ራሔልም አባቷን “ጌታዬ በወር አበባዬ ምክንያት መነሣት ስላልቻልኩ ቅር አትሰኝብኝም” አለችው። ላባ በሁሉ ስፍራ ፈልጎ ጣዖቶቹን ማግኘት አልቻለም።
ዘሌዋውያን 19:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዕድሜ የገፉ ሽማግሌዎች ሲመጡ ስታይ ከተቀመጥክበት በመነሣት አክብራቸው፤ እኔን አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሽበታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማግሌውንም አክብር፤ አምላክህን እግዚአብሔርንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
ራሔልም አባቷን “ጌታዬ በወር አበባዬ ምክንያት መነሣት ስላልቻልኩ ቅር አትሰኝብኝም” አለችው። ላባ በሁሉ ስፍራ ፈልጎ ጣዖቶቹን ማግኘት አልቻለም።
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
በታላቅ ኀይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፤
ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።
ሕዝቡም እርስ በርሱ አንዱ ሌላውን ለመጨቈን ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ ይነሣሣል፤ ወጣቱ ሽማግሌውን አያከብርም፤ ተንቆ ይኖር የነበረውም ሰው ክብር ባለው ሰው ላይ ይታበያል።
እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።