Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 32:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤ እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ ፈርቼ ዝም አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ በዕ​ድ​ሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እና​ንተ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ናችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ዕው​ቀ​ቴን እገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 32:6
14 Referencias Cruzadas  

“ጥበብ በሽምግልና፥ ማስተዋልም በዕድሜ መርዘም ይገኛሉ።


በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ ጠጒራቸው የሸበተ ሽማግሌዎች በሐሳብ ከእኛ ጋር ናቸው።


“ከሰው በፊት የተወለድክ አንተ ነህን? ተራራዎችስ ከመፈጠራቸው በፊት ተወልደህ ነበርን?


የራም ቤተሰብ የነበረው ቡዛዊው የባራኬል ልጅ ኤሊሁ ኢዮብ ራሱን ከእግዚአብሔር አብልጦ ጻድቅ ስላደረገ ተቈጣ።


ሦስቱ ሰዎች ለኢዮብ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት አለመቻላቸውን በማየቱ እጅግ ተቈጣ።


ኤሊሁም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦


ኤሊሁም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦


ኤሊሁ አሁንም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦


“በዕድሜ የገፉ ሽማግሌዎች ሲመጡ ስታይ ከተቀመጥክበት በመነሣት አክብራቸው፤ እኔን አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።


ሽማግሌን እንደ አባት አድርገህ ምከረው እንጂ አትገሥጸው፤ ወጣቶች ወንዶችን እንደ ወንድሞች፥


እንዲሁም ጐልማሶች ራሳቸውን በመቈጣጠር እንዲኖሩ ምከራቸው።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos