Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 32:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ በዕ​ድ​ሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እና​ንተ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ናችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ዕው​ቀ​ቴን እገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤ እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ ፈርቼ ዝም አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 32:6
14 Referencias Cruzadas  

በዕ​ድሜ ከአ​ባ​ትህ የሚ​በ​ልጡ፥ ሽበ​ትም ያላ​ቸው ሽማ​ግ​ሎች ከእኛ ጋር አሉ።


ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፤ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፥ ቆነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና ለምናቸው።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።


ለሁ​ሉም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው አድ​ርጉ፤ ግብር ለሚ​ገ​ባው ግብ​ርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚ​ገ​ባው ቀረ​ጥን ስጡ፤ ዐሥ​ራት ለሚ​ገ​ባው ዐሥ​ራ​ትን ስጡ፤ ሊፈ​ሩት የሚ​ገ​ባ​ውን ፍሩ፤ ክብር የሚ​ገ​ባ​ው​ንም አክ​ብሩ።


በውኑ ከሰው ቀድ​መህ የተ​ፈ​ጠ​ርህ ሰው አንተ ነህን? ወይስ ከተ​ራ​ሮች በፊት ተፀ​ነ​ስ​ህን?


“በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


ከአ​ው​ስ​ጢድ ሀገር ከአ​ራም ወገን የሆነ የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤሊ​ዩስ ተቈጣ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድ​ርጎ ነበ​ርና ኢዮ​ብን ተቈ​ጣው።


ኤሊ​ዩ​ስም በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስቱ ሰዎች አፍ መልስ እን​ደ​ሌለ ባየ ጊዜ በቍ​ጣው ተቈ​ጣ​ቸው።


በረ​ዥም ዘመን ጥበብ፥ በመ​ኖር ብዛ​ትም ዕው​ቀት ይገ​ኛል።


ኤል​ዩስ ደግሞ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


ኤል​ዩ​ስም ደግሞ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


ኤል​ዩ​ስም ደግሞ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios