ኢዮብ 32:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤ እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ ፈርቼ ዝም አልሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፥ “እኔ በዕድሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ዕውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ። Ver Capítulo |