ነገር ግን ሙሴ “ወገኖቼ እስራኤላውያን እንኳ አልሰሙኝም፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል? እንደምታየኝ እኔ ኰልታፋ ነኝ” ሲል መለሰ።
ዘሌዋውያን 19:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወደ ከነዓን ምድር ገብታችሁ ማንኛውንም ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ እስከ መጀመሪያው ሦስት ዓመት ድረስ የሚሰጠውን ፍሬ መብላት የተከለከለ መሆኑን አስታውሱ። በእነዚህም ዓመቶች ውስጥ ፍሬው አይበላም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ወደ ምድሪቱ ገብታችሁ ማንኛውንም ዐይነት ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ፣ ፍሬው ለመብላት ያልተገረዘ መሆኑን ዕወቁ፤ ለሦስት ዓመትም የተከለከለ በመሆኑ አይበላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወደ ምድሪቱም ገብታችሁ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁ ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት ለእናንተ እንዳልተገረዘ ይሆናል፤ አይበላም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ ከርኵሰቱ ሁሉ ታጠሩታላችሁ፤ የሦስቱ ዓመት ፍሬም ርኩስ ነው፤ አይበላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አገሩም በገባችሁ ጊዜ፥ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁም ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት እንዳልተገረዘ ይሆንላችኋል፤ አይበላም። |
ነገር ግን ሙሴ “ወገኖቼ እስራኤላውያን እንኳ አልሰሙኝም፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል? እንደምታየኝ እኔ ኰልታፋ ነኝ” ሲል መለሰ።
እኔም መልሼ እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ብነግራቸውና ባስጠነቅቃቸው ማን ሊሰማኝ ይችላል? እነርሱ እልኸኞች ስለ ሆኑ፥ ቃልህን መስማት አይፈልጉም፤ የአንተን ቃል ስነግራቸው በንቀት መሳቂያ ያደርጉኛል።
“እንቦሳ፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ሲወለድ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ መቅረብ ይችላል።
ይህንንም ስጦታ ለእግዚአብሔር ከማቅረባችሁ በፊት ከአዲሱ እህል ጥሬውን ወይም የተቈላውን ወይም እንጀራ ጋግራችሁ አትብሉ። ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በልጅ ልጆቻችሁ ተጠብቆ ይኑር።