ዘሌዋውያን 13:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ቊስሉ ነጭ ሆኖ በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጐድ ብሎ ባይገኝና ጠጒሩም ወደ ነጭነት ባይለወጥ፥ ካህኑ ያን ሰው ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቈዳው ላይ ያለው ቋቍቻ ነጭ ሆኖ ቢታይ፣ ነገር ግን ከቈዳው በታች ዘልቆ ባይገባና በቦታው ላይ የሚገኘው ጠጕር ወደ ነጭነት ባይለወጥ፣ ካህኑ በሽተኛውን ሰባት ቀን ያግልለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ቋቁቻው በሰውነቱ ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ በእርሱም ላይ ያለው ጠጉር ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቋቍቻውም በሥጋው ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆዳውም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጕሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍቁቻውም በሥጋው ቁርበት ላይ ቢነጣ፥ ከቁርበቱም የጠለቀ ባይመስል፥ ጠጉሩም ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይዘጋበታል። |
እርሱ በቈዳው ላይ የቈየ የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ካህኑ ሕመምተኛው የረከሰ መሆኑን ያስታውቅ፤ የረከሰ መሆኑ በግልጥ ስለ ታወቀ እንደዚህ ያለው ሰው በቤት ውስጥ ተዘግቶበት መቈየት አያስፈልገውም።
ካህኑ ይመርምረው፤ ቊስሉ ባለበት ስፍራ የበቀለው ጠጒር ነጭ ቢሆንና ያም ስፍራ በዙሪያው ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ከተገኘ፥ ከእሳት ቃጠሎ የመጣ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ስለዚህም ካህኑ ያ ሰው የረከሰ መሆኑን ያስታውቅ። ይህም የሥጋ ደዌ ነው።
ነገር ግን በእርሱ ላይ የበቀለው ጠጒር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ በዙሪያውም ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ካልተገኘና የቀለም መለዋወጥ ብቻ ሆኖ ከተገኘ፥ ካህኑ ያ ሰው ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ።
ካህኑም ቊስሉን ይመርምር፤ በዚያም ቊስል ላይ ያለው ጠጒር ወደ ነጭነት ቢለወጥ፥ ቊስሉም በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ቢገኝ፥ እርሱ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው፤ ካህኑም ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።
ነገር ግን ካህኑ ሲመረምረው የሚያሳክከው ቊስል በዙሪያው ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ የማይታይ ከሆነና በላዩ ላይ ያለው ጠጒር ጤናማ ካልሆነ፥ በሚያሳክከው ቊስል ምክንያት ያ ሰው በቤት ውስጥ ተዘግቶበት ለሰባት ቀን እንዲቈይ ያድርግ፤
ካህኑ በሰባተኛው ቀን እንደገና ይመርምረው፤ በሚመረምረውም ጊዜ ቊስሉ ምንም ለውጥ ሳያሳይ እንደ ነበረ ሳይስፋፋ ቢያገኘው፥ አሁንም ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ላይ ቢተፋባት እንኳ ኀፍረትዋን ተሸክማ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ትቈይ የለምን? ስለዚህም እርስዋ ከሰፈር ወጥታ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በገለልተኛ ቦታ ትቈይ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሳ ወደ ሰፈር ልትገባ ትችላለች።”
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።