ዘሌዋውያን 11:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው ነገር ሁሉ የእነዚህ እንስሶች በድን ሲነካው የሚረክስ ቢሆንም ምንጭ ወይም የውሃ ጒድጓድ አይረክስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ምንጭ ወይም የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ንጹሕ እንደ ሆነ ይቈያል፤ ሆኖም በድኑን የነካ ይረክሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ምንጭና የውኃ ማጠራቀምያ ጉድጓድ ንጹሕ ይሆናሉ፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ምንጩ፥ ጉድጓዱም፥ የውኃውም ኵሬ ንጹሓን ናቸው፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ምንጩ፥ ጕድጓዱም፥ የውኃውም ኩሬ ንጹሐን ናቸው፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ነው። |
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”