እንዲሁም በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፤ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት።
ዘሌዋውያን 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው፤ እንዲህ ብሎም አዘዘው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው፤ ከመገናኛውም ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛው ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከምስክሩ ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፦ |
እንዲሁም በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፤ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት።
በዚህ ዐይነት ሕዝቡ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ያመጡአቸው እንስሶች ብዛት ሰባ ኰርማዎች፥ አንድ መቶ የበግ አውራዎችና ሁለት መቶ የበግ ጠቦቶች ነበሩ።
ሙሴም ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ ተራራው ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከተራራው ላይ በመናገር የያዕቆብ ተወላጆች ለሆኑት እስራኤላውያን እንዲህ ብሎ እንዲናገር አዘዘው፥
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ወዳለሁበት ወደ ተራራው ወጥተህ በዚያ ቈይ፤ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችንም እሰጥሃለሁ፤ በእነርሱም ላይ ለሕዝቡ መመሪያዎች ይሆኑ ዘንድ እኔ የጻፍኳቸው ትእዛዞችና ኅጎች ይገኛሉ።”
እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።
ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መቅረብ አለበት፤ እኔ ሕዝቤን የምገናኘውና አንተንም የማነጋግርበት ስፍራ ይኸው ነው።
ሙሴም ሁኔታውን ለማየት በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር ተመለከተው፤ በቊጥቋጦውም መካከል ሆኖ “ሙሴ! ሙሴ!” ብሎ ጠራው። ሙሴም “እነሆ፥ አለሁ” አለ።
የእስራኤል ሕዝብ በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ ሙሴ ድንኳኑን ከሰፈሩ ራቅ ባለ ቦታ ይተክለው ነበር፤ እርሱም “ድንኳን” ተብሎ ተጠራ፤ እግዚአብሔርን መጠየቅ የሚፈልግ ሁሉ ወደዚያ ይሄድ ነበር።
እዚያም በድንኳኑ መግቢያ ፊት ለፊት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ አኖረ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቊርባን እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእርሱ ላይ አቀረበ፤
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን በሲና በረሓ ሳሉ፥ እግዚአብሔር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን እንዲህ ሲል አነጋገረው፦
ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በኪሩቤል መካከል ካለው ከቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ በላይ ሆኖ ሲናገረው ሰማ።