ሰቈቃወ 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም ቅጥር ውስጥ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር ጩኹ! ዕንባችሁም ሌሊትና ቀን እንደ ጐርፍ ይውረድ፤ በፍጹም ዕረፍት አታድርጉ፤ ለዐይኖቻችሁም ፋታን አትስጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቡ ልብ፣ ወደ ጌታ ጮኸ። የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፤ ቀንና ሌሊት፣ እንባሽ እንደ ወንዝ ይፍሰስ፤ ለራስሽ ዕረፍትን አትስጪ፣ ዐይኖችሽ ከማንባት አያቋርጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዐይንሽ ብሌን አታቋርጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፤ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፤ የዐይንሽንም ብሌን አታቋርጪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዓይንሽ ብሌን አታቋርጥ። |
አናዳምጥም ብትሉ ግን ስለ ትዕቢታችሁ ተደብቄ አለቅሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምርኮኞች ሆነው በመወሰዳቸውም ምርር ብዬ አለቅሳለሁ፤ እንባዬም ባለማቋረጥ ይፈስሳል።
ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ። “ሕዝቤ እጅግ ቈስሎአል፤ በብርቱም ተጐድቶአል፤ ስለዚህ ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት እንባ ያፈሳሉ፤ ባለማቋረጥም አለቅሳለሁ።
ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።
በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጒንጮችዋ ላይ ይወርዳል፤ ከአፍቃሪዎችዋ ሁሉ እርስዋን የሚያጽናና አንድ እንኳ የለም፤ ወዳጆችዋ የነበሩ ሁሉ ከድተዋታል፤ በጠላትነትም ተነሥተውባታል።
እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ።
በአልጋቸው ላይ ተጋድመው ይጮኻሉ እንጂ ከልባቸው ወደ እኔ አይጸልዩም፤ እህልና የወይን ጠጅ ለማግኘት ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤ በእኔም ላይ ያምፃሉ።