ሕዝቡ በፈቃዳቸውና በሙሉ ልብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፤ እጅግ ብዙ ሀብት ገቢ በመሆኑም ደስ አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም ከመጠን በላይ ደስ ተሰኘ።
መሳፍንት 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤ ከእስራኤል የጦር አዛዦች ጋር ነው፤ እንዲሁም ደስ ብሎአቸው በበጎ ፈቃድ ከተነሣሡት ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ይመስገን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋራ ነው፤ እግዚአብሔር ይመስገን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ነው፥ በሕዝቡ መካከል ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ወደ ሰጡት፥ ጌታን አመስግኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቤ ለእስራኤል ወደ ታዘዘው ትእዛዝ ነው፤ እናንተ የእስራኤል ኀያላን፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ነው፥ በሕዝቡ መካከል ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ወደ ሰጡት፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ። |
ሕዝቡ በፈቃዳቸውና በሙሉ ልብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጡ፤ እጅግ ብዙ ሀብት ገቢ በመሆኑም ደስ አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም ከመጠን በላይ ደስ ተሰኘ።
ከይሆሐናን ቀጥሎ በማዕርግ ሦስተኛ የሆነው የጦር መኰንን የዚክሪ ልጅ ዐማሥያ ነበር፤ በእርሱም ሥር ሁለት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የለየ የጦር አዛዥ ነበር፤
ንጉሥ ሕዝቅያስና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች መጥተው፥ እጅግ የበዛውን የስጦታ ክምር ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔርንና የእርሱ ወገኖች የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ አመሰገኑ፤
ስለዚህ ልትሰጡ ቃል የገባችሁበትን የልግሥና ስጦታችሁ በቅድሚያ እንድታዘጋጁ እንዲያስታውሱአችሁ በማለት እነዚህ ወንድሞች ከእኔ ቀድመው ወደ እናንተ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በምመጣበት ጊዜ የልግሥና ስጦታችሁ ዝግጁ ይሆናል፤ እናንተም የምትሰጡት በግድ ሳይሆን በፈቃደኛነት መሆኑን ያሳያል።