ኢያሱ 8:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ለኢያሱ በነገረው መሠረት እስራኤላውያን በዚያች ያገኙትን የከብትና የሌላ ንብረት ምርኮ ሁሉ ለራሳቸው አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት፣ በከተማዪቱ ያገኙትን እንስሳትና ምርኮ ብቻ ለራሳቸው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጌታ ኢያሱን ባዘዘው ቃል መሠረት የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ብቻ እስራኤል ለራሳቸው ዘረፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ሁሉ የእስራኤል ልጆች ለራሳቸው ዘረፉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው ቃል የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ እስራኤል ለራሳቸው ዘረፉ። |
እንደ ወርቅ፥ ብር፥ ነሐስ፥ ብረት፥ ቆርቆሮ ወይም እርሳስ የመሳሰሉ እሳት የማይጐዳቸው ነገሮች በእሳት ውስጥ አልፈው መጥራት ይኖርባቸዋል፤ እሳት መቋቋም የማይችለውን ነገር ሁሉ ለመንጻት ሥርዓት በተመደበው ውሃ ታጠሩታላችሁ።
ከዚህ በፊት በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ የደረሰውን ጥፋት በዐይና በንጉሥዋም ላይ ደግሞ ትፈጽምባቸዋለህ፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከእርስዋ የሚገኘውን የንብረትና የከብት ምርኮ ለራሳችሁ ታደርጋላችሁ፤ ከኋላ በኩል በከተማይቱ ላይ በድንገት አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።”