ኢያሱ 6:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበር የኢያሱ ዝና በአገሪቱ ሁሉ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር ከኢያሱ ጋራ ነበር፤ ዝናውም በምድሪቱ ሁሉ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ከኢያሱ ጋር ነበረ፤ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበረ፤ ስሙም በምድር ሁሉ ላይ ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበረ፥ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ። |
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ወደፊትም በተራመድህ መጠን ጠላቶችህን ድል አደረግሁልህ፤ ገና ደግሞ በዓለም እንደ ታወቁት ታላላቅ መሪዎች ዝነኛ አደርግሃለሁ።
መርዶክዮስ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት ውስጥ በቤተ መንግሥት ከፍተኛ ሥልጣን የተሰጠው ታላቅ ሰው መሆኑና ኀይሉም እየበረታ መሄዱ በደንብ ታወቀ።
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ቈራጥነትና ድፍረት ይኑራችሁ፤ ከእነርሱም የተነሣ ከቶ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ አይጥላችሁም፤ አይተዋችሁም።”
አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤
ከዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቈላማው አገሮች፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ፥ እስከ ሊባኖስ ድረስ ያሉት የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፔሩዛውያን የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፥
እግዚአብሔር ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ስለ ነበረ የተራራማውን አገር አሸንፈው ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ሜዳ አገር የነበሩት ኗሪዎች የብረት ሠረገሎች ስለ ነበሩአቸው ሊያስወጡአቸው አልቻሉም።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።