ኢያሱ 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ ባለው ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፥ ከወሩ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በኢያሪኮ ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፣ ወሩ በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ ምዕራብ ፋሲካን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፥ ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ። |
ለጒዞ እንደ ተዘጋጀ ሰው ሆናችሁ ወገባችሁን በመታጠቅ ጫማችሁን አድርጋችሁ፥ በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ በችኰላ ብሉት፤ እርሱም እኔን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።
ነገር ግን የባቢሎን ሠራዊት ከኋላቸው ተከትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ ደረሱበትና ሴዴቅያስን ማረኩት፤ ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሥ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያን ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር በሐማት ግዛት ሪብላ ተብላ በምትጠራ ከተማ ውስጥ ነበር፤ ንጉሥ ናቡከደነፆርም እዚያው በሴዴቅያስ ላይ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈበት።
“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ! የስደት ዕቃህን ጠቅልለህ አዘጋጅ፤ እነርሱ እያዩም የስደት ጒዞህን በቀን ጀምር፤ እንደ ስደተኛ ከቦታህ ተነሥተህ ወደ ሌላ ቦታ ሂድ፤ ዐመፀኞች ቢሆኑም እንኳ ያስተውሉ ይሆናል።
ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”
ይህን ሁሉ ካደረጉ በኋላ በጌልገላ ወደሚገኘው ሰፈር ሄደው ኢያሱንና እስራኤላውያንን፦ “እኛ የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ የመጣነውም ከእናንተ ጋር የቃል ኪዳን ውል ለማድረግ ነው” አሉአቸው።