‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ኢያሱ 19:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ሕዝብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። በዚህም ዐይነት ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የየጐሣ መሪዎች ሴሎ ላይ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ያደላደሉት ርስት ይህ ነው፤ የምድሪቱንም አከፋፈል በዚህ ሁኔታ ፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በጌታ ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም አከፋፍለው ጨረሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ጨረሱ። |
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ኢየሱስም “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን ሰዎችን በቀኜና በግራዬ እንዲቀመጡ የማደርገው እኔ አይደለሁም፤ ይህ ቦታ የሚሰጠው አባቴ ላዘጋጀላቸው ሰዎች ነው።”
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የቤተሰብ አለቆች በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን አከፋፍለዋቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው።
ከዚህ በኋላ “በየዓመቱ በሴሎ ለእግዚአብሔር የሚዘጋጀው በዓል እነሆ ቀርቦአል” በማለትም አሰቡ፤ ሴሎ ከቤትኤል በስተ ሰሜን፥ ከለቦና በስተ ደቡብ፥ በቤትኤልና በሴኬም መካከል ካለው መንገድ በስተ ምሥራቅ ነበረች።
ተጠባበቁ፤ በበዓሉ ዕለት የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር ሲመጡ እናንተም ከወይኑ ተክል ውስጥ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ከእነዚያ ልጃገረዶች መካከል እየጠለፋችሁ ሚስት አድርጋችሁ ውሰዱ፤ ወደ ብንያም ግዛትም ይዛችኋቸው ሂዱ።
ሕልቃና በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ሴሎ ይሄድ ነበር፤ በዚያም ዘመን ሖፍኒና ፊንሐስ ተብለው የሚጠሩት የዔሊ ልጆች የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው በሴሎ ያገለግሉ ነበር።