ኢያሱ 19:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። |
ስለ ንፍታሌም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በጌታ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነው፤ በእግዚአብሔር በረከትም ተሞልቶአል፤ ግዛቱም እስከ ባሕሩና ወደ ደቡብ የተዘረጋ ነው።”
ድንበሩም ከሔሌፍ በመነሣት በአዳሚኔቄብና በያሚኒያ በኩል መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ እስከ ላቁም ድረስ እስከ ዳዕናኒም ወርካ ይዘልቃል።
የንፍታሌም ነገድ በቤትሼሜሽና በቤትዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡም፤ ስለዚህም የንፍታሌም ሕዝብ ከከነዓናውያን ጋር እዚያው አብረው መኖርን ቀጠሉ፤ ሆኖም የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ከነዓናውያንን ያስገድዱአቸው ነበር።
የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤