ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቊጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
ኢያሱ 19:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዑማ፥ አፌቅና ረሖብ ተብለው የሚጠሩትን ኻያ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ይጨምራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የዑማን፣ የአፌቅንና የረአብን ምድር ይጨምራል። በዚህም ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረዓብ ደግሞ ነበሩ፤ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርኮብ፥ አፌቅ፥ ረአውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ፥ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቊጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
በሌላም በኩል የሲዶናውያን ይዞታ የሆነው የከነዓን አገር መዓራ ተብሎ የሚጠራውን ሁሉ ጨምሮ በአሞራውያን ጠረፍ እስከ አፌቅ ድረስ የሚገኘው፥
ድንበሩ እስከ ተመሸገችው እስከ ጢሮስ ከተማ ይደርስና ወደ ራማ ይታጠፋል፤ ከዚያም መመለሻው የሜድትራኒያን ባሕር ሆኖ ወደ ሖሳ ይታጠፋል፤ እርሱም ማሐላብ፥ አክዚብ፥
እስራኤላውያን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ሳሉ፥ ፍልስጥኤማውያን ወታደሮቻቸውን በአንድነት ሰብስበው በማምጣት በአፌቅ አሰለፉ፤
እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ስለዚህም እስራኤላውያን አቤንዔዜር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም አፌቅ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤