አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።
ዮናስ 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ዮናስን፣ “በውኑ ስለ ቅሉ ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም፣ “በርግጥ እስከ ሞት ልቈጣ ይገባኛል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “በውኑ ስለዚች ቅል ታዝናለህን?” አለው። እርሱም፥ “እስክሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ” አለ። |
አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “አንተ በአንድ ቀን በቅላ፥ በአንድ ቀን ለደረቀች፥ እንዲያውም ላልደከምክባትና ላላሳደግሃት ተክል ይህን ያኽል አዝነሃል!
ፀሐይ ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ ላከ፤ የፀሐዩም ሐሩር ራሱን ስላቃጠለው ዮናስ ተዝለፈለፈ፤ ሞትንም በመመኘት “ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል” አለ።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ሐዘን ወደ መዳን የሚመራ በንስሓ የሚገኘውን ለውጥ ስለሚያስገኝ ጸጸትን አያስከትልም፤ ዓለማዊ ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።