ዮናስ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነነዌ ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል አመኑ፤ ጾምም ዐወጁ፤ መጸጸታቸውንም ለመግለጥ ከታላላቅ ጀምሮ እስከ ታናናሽ ድረስ ሁሉም ማቅ ለበሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፤ ሰዎቹም ሁሉ ከትልቁ እስከ ትንሹ ማቅ ለበሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነነዌም ሰዎች በእግዚአብሔር አመኑ፤ ጾምም አወጁ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። |
ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤
እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።
መርዶክዮስም ስለ ተደረገው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከዚህም በኋላ ማቅ ለብሶና በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ እየጮኸ በመረረ ሁኔታ በማልቀስ ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገባ።
ከእንግዲህ ወዲህ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ ባልንጀራውንም ሆነ ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤ ከትልቁ ጀምሮ እስከ ትንሹ ሁሉም ያውቁኛል፤ በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንም አላስታውስባቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብና ከይሁዳ ከተሞች የመጡት ሕዝብ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ለማግኘት የጾም ጊዜ አወጁ።
የተለየ የጾም ቀን ዐውጁ! መንፈሳዊ ስብስባ ጥሩ! ሽማግሌዎችንና ሌሎችንም የአገሪቱን ኗሪዎች ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ በዚያም ወደ እግዚአብሔር ጩኹ።
ለነነዌም ሕዝብ እንዲህ ሲል ዐዋጅ አስነገረ፥ “ከንጉሡና ከመኳንንቱ በተላለፈው ትእዛዝ መሠረት፥ ማንም ሰው ወይም እንስሳ፥ የከብትም ሆነ የበግ መንጋ አንዳች ምግብ አይቅመሱ፤ ውሃም አይጠጡ፤
የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋልና። አሁን ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።
እንዲሁም የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋል፤ ነገር ግን እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።”
እምነት ማለት በተስፋ የሚጠበቀውን ነገር “አዎን በእውነት ይሆናል” ብሎ መቀበል ነው፤ በዐይን የማይታየውንም ነገር እንደሚታይ አድርጎ መቊጠር ነው።
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።