ዮሐንስ 4:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፦ “መምህር ሆይ! አንዳች ምግብ ብላ” ሲሉ ለመኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ፣ “ረቢ፣ እህል ቅመስ እንጂ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሲሆን ሳለ ደቀመዛሙርቱ “መምህር ሆይ! ብላ፤” ብለው ለመኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ፥ “መምህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ሲሆን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ፦ መምህር ሆይ፥ ብላ ብለው ለመኑት። |
ጴጥሮስም ኢየሱስን፦ “መምህር ሆይ! እዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ለኤልያስ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች እንሥራ” አለው።
ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና “ምን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “ረቢ! የምትኖረው የት ነው?” አሉት። (ረቢ ማለት መምህር ማለት ነው)
ደቀ መዛሙርቱም “መምህር ሆይ! አይሁድ ከጥቂት ጊዜ በፊት ሊወግሩህ ይፈልጉ ነበር፤ ታዲያ እንደገና ወደዚያ ተመልሰህ ትሄዳለህን?” አሉት።
ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በቀር እነዚህን አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል ማንም የለም፤ ስለዚህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንክ እናውቃለን” አለው።
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ዮሐንስ ቀርበው “መምህር ሆይ፥ ያ ከዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው፥ አንተ ስለ እርሱ የመሰከርክለት፥ እነሆ፥ እርሱም ያጠምቃል፤ ሰዎችም ሁሉ ወደ እርሱ ይሄዳሉ” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነውን ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት።