ዮሐንስ 19:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያየ፥ እናንተ እንድታምኑ መሰከረ፤ ምስክርነቱም እውነት ነው፤ የሚናገረውም እውነት እንደ ሆነ፥ እርሱ ያውቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያየው ሰው ምስክርነቱን ሰጥቷል፤ ምስክርነቱም እውነት ነው፤ እውነትን እንደሚናገርም ያውቃል፤ እናንተም እንድታምኑ ይመሰክራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያየውም መስክሮአል፤ ምስክርነቱም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንደሚናገር ያውቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያየውም መሰከረ፤ ምስክርነቱም እውነት ነው፤ እርሱም እናንተ ልታምኑ እውነት እንደሚናገር ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያየውም መስክሮአል፤ ምስክሩም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል። |
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር አብሬ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የሆንኩ፥ የክርስቶስም መከራ ምስክር የሆንኩ፥ እንዲሁም ወደፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፥ በመካከላችሁ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ።
ለድሜጥሮስ ሰው ሁሉ በመልካም ይመሰክርለታል። እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች። እኛም እንመሰክርለታለን፤ የእኛም ምስክርነት እውነት መሆኑን ታውቃለህ።