ዮሐንስ 19:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ ገረፈው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። |
እርሱ ግን ተወግቶ የቈሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው፤ እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን።
ስለዚህ እነሆ፥ እኔ ነቢያትን፥ ጥበበኞችን፥ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹንም በምኲራባችሁ ትገርፋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዱአቸዋላችሁ