ዮሐንስ 15:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን ከአብ የሚወጣና እኔም ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኙ የእውነት መንፈስ ሲመጣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ፣ ከአብ የሚወጣው አጽናኙ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ፥ እርሱም ከአብ የሚወጣው የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ |
እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንማ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የላከኝ እርሱ ነው እንጂ እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም።
እግዚአብሔርም ደግሞ ምልክቶችን፥ ድንቅ ነገሮችን፥ ልዩ ልዩ ተአምራትን በማድረግና እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቸውን አጽንቶአል።