‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ዮሐንስ 11:52 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሞተውም ስለ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን፥ የተበተኑትንም የእግዚአብሔርን ልጆች በአንድነት ለመሰብሰብ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዚያም ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች በአንድነት ለመሰብሰብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ሕዝብ ብቻ አልነበረም፤ የተበተኑትን የእግዚአብሔርንም ልጆች በአንድነት ይሰበስባቸው ዘንድ ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ። |
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ቀና ብለሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ ልጆችሽ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እንዲህ እላለሁ፦ ‘ሁሉንም እንደ ልብስ ትለብሺአቸዋለሽ፤ ሙሽራ በጌጣጌጥ እንደምታጌጥ አንቺም በእነርሱ ታጌጪአለሽ።’
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”
የተበተኑትን እስራኤላውያንን የሚሰበስበው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከተሰበሰቡት ሌላ ሌሎችንም ወገኖች ወደ እነርሱ ሰብስቤ አመጣቸዋለሁ።”
ቀና ብለሽ በዙሪያሽ ያለውን ሁኔታ ተመልከቺ! ሁላቸውም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽም በሞግዚቶቻቸው ክንድ ሆነው ወደ አንቺ ይመጣሉ።
የበግ እረኞች ከተበታተኑት በጎቻቸው መካከል መንጋዎቻቸው እንደሚፈለጉ፥ እኔም በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበታተኑበት ቦታ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ዐሥር የብር መሐለቅ ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ መሐለቅ ቢጠፋባት መብራት አብርታ፥ ቤትዋን ጠርጋ የጠፋባትን መሐለቅ እስክታገኝ ድረስ በጥንቃቄ አትፈልገውምን?
በዚህ መንጋ ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት ይገባኛል፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ ይሆናል።
ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር።
በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው ከያዕቆብ የተላከ መልእክት፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፥ መጻተኞች ሆናችሁ በጳንጦስ፥ በገላትያ፥ በቀጰዶቅያ፥ በእስያ፥ በቢታንያ ተበታትናችሁ ለምትኖሩት
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ! በእርግጥም የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዓለም እግዚአብሔርን ስላላወቀ እኛንም አያውቀንም።
የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፦ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤