Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 18:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በዚህች ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝና ጒዳት ሊያደርስብህ የሚችል ማንም የለም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና ማንም በአንተ ላይ ተነሥቶ ሊጐዳህ አይችልም፤ በዚህች ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝና።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ማንም ሊጐ​ዳህ የሚ​ነ​ሣ​ብህ የለም፤ በዚች ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉ​ኝና።”

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 18:10
26 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።


ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምሩአቸው! እነሆ፥ እኔም እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።


ስለዚህ አሁን ሂድ! እኔም ከአንተ ጋር ሆኜ መናገር እንድትችል አደርጋለሁ፤ ምን መናገር እንደሚገባህ እነግርሃለሁ።”


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?


በዚህ መንጋ ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት ይገባኛል፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ ይሆናል።


ጌታ ከአንተ ጋር ይሁን። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።


የሚሞተውም ስለ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን፥ የተበተኑትንም የእግዚአብሔርን ልጆች በአንድነት ለመሰብሰብ ነው።


የእናንተ ግን የራስ ጠጒራችሁ እንኳ የተቈጠረ ነው።


በምትሄድበት ሁሉ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለምሆን አይዞህ! በርታ! አትፍራ! ብዬ አዝሃለሁ።”


ከጥንት ጀምሮ ይህን ሁሉ ያስታወቅኹ እኔ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፤’


ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዲት እንኳ አትጠፋም።


በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


የጦር ዕቅድንም አውጡ፤ ነገር ግን እናንተ እንዳሰባችሁት አይሳካላችሁም፤ የፈለጋችሁትን ያኽል ተናገሩ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምክራችሁ አይጸናም።


እግዚአብሔር አንድ በስሙ የሚጠራ ሕዝብን ከመካከላቸው ለመምረጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አሕዛብን እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን አስረድቶአል።


እግዚአብሔር መስፍን ባስነሣላቸው ጊዜ ሁሉ እርሱ ከመስፍኑ ጋር ነበር፤ በሚያሳድዱአቸውና በሚጨቊኑአቸው ጠላቶች ምክንያት ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ያዝንላቸው ስለ ነበረ በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር።


አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤


ጌታም ጳውሎስን ሌሊት በራእይ እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፤ ተናገር፤ ዝም አትበል፤


ስለዚህ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል ለሕዝቡ እያስተማረ አንድ ዓመት ተኩል እዚያ ቈየ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios