በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ እኔ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍራ፤ ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ” አለው።
ዮሐንስ 11:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ እንድታምኑ እዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ብሎኛል፤ አሁን ግን ወደ እርሱ እንሂድ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታምኑ ዘንድ፣ በዚያ ባለ መኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ አሁን ግን ወደ እርሱ እንሂድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታምኑም ዘንድ እኔ በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ኑ፥ ወደ እርሱ እንሂድ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ” አላቸው። |
በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ እኔ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍራ፤ ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ” አለው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወይን ጠጅ ከወይን ዘለላ እንደሚገኝና ‘በረከት ስላለበት አታጥፉት’ እንደሚባል እኔም በዚሁ ዐይነት ስለ አገልጋዮቼ ስል ሕዝቡን በሙሉ አላጠፋም።
ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ሕመም ለሞት የሚያደርስ አይደለም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆንና የእግዚአብሔር ልጅም በዚህ ምክንያት እንዲከበር ነው” አለ።
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ስለዚህ እነርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘውን መዳንና ዘለዓለማዊ ክብርን እንዲያገኙ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ስል ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።