Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም የሆነው ጸጋ ተትረፍርፎ ለብዙ ሰዎች በደረሰ መጠን ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆነው ምስጋና እንዲበዛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ለብዙ ሰዎች እየደረሰ ያለው ጸጋ፣ ለእግዚአብሔር ክብር በምስጋና ላይ ምስጋናን እንዲጨምር ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሆኗል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ፥ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን እንዲያበዛ፥ ሁሉም ነገር ስለ እናንተ ሆኗል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጸጋው በብ​ዙ​ዎች ላይ ትት​ረ​ፈ​ረፍ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የክ​ብሩ ምስ​ጋና ይበዛ ዘንድ ሁሉ ስለ እና​ንተ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 4:15
21 Referencias Cruzadas  

የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።


የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።”


እግዚአብሔርን ለሚወዱና እንደ ፈቃዱም ለተጠሩት ሰዎች እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለበጎ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።


እኔ የማንም ባሪያ ሳልሆን ነጻ ሰው ነኝ፤ ይሁን እንጂ በተቻለኝ መጠን ብዙዎቹን በማዳን ለመጥቀም ብዬ የሁሉም ባሪያ ሆኜአለሁ።


እናንተም እኛን በጸሎት ልትረዱን ይገባል፤ በብዙ ጸሎት እኛ የእግዚአብሔርን ርዳታ ስናገኝ ብዙ ሰዎች ደግሞ በእኛ ምክንያት እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።


ከዚህም በላይ ይህ ወንድም እኛ ይህን በጎ ሥራ ለጌታ ክብር ስንፈጽምና ለማገልገል ያለንንም መልካም ፈቃድ ስንገልጥ አብሮን በመሄድ የሥራ ተካፋያችን እንዲሆን በአብያተ ክርስቲያን የተመረጠ ነው።


በእኔ ምክንያትም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።


አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።


የአምላካችን ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የእኛ ከሆነው እምነትና ፍቅር ጋር ተትረፍርፎ ተሰጠኝ።


ስለዚህ እነርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘውን መዳንና ዘለዓለማዊ ክብርን እንዲያገኙ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ስል ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


የሚያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያስተምር ያስተምር፤ የሚያገለግልም እግዚአብሔር በሚሰጠው ኀይል ያገልግል፤ በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሁሉ ነገር ይመሰገናል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos