ዮሐንስ 1:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እንድርያስ ስምዖንን ወደ ኢየሱስ አመጣው። ኢየሱስም ትኲር ብሎ ተመለከተውና “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ኬፋ ትባላለህ” አለው። (ኬፋ ማለት ጴጥሮስ ወይም አለት ማለት ነው።) አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመለከተውና፣ “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ተብለህ ትጠራለህ” አለው፤ “ኬፋ” ማለት ጴጥሮስ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ” አለው፤ ትርጓሜውም “ጴጥሮስ” ማለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መጀመሪያ ወንድሙ ስምዖንን አግኝቶ “በትርጓሜው ክርስቶስ የሚሉት መሲሕን አገኘነው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው። |
የዐሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ዝርዝር፥ እንደሚከተለው ነው፦ መጀመሪያ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፥ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ፥
ይህን የምናገረው ስለ ሁላችሁም አይደለም፤ እኔ የመረጥኳችሁን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ‘እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሣብኝ’ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም አለበት።
ጳውሎስም ቢሆን አጵሎስም ቢሆን፥ ጴጥሮስም ቢሆን፥ ዓለምም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ አሁን ያለውም ቢሆን፥ በኋላ የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉም የእናንተ ነው።
እንደ ምሰሶ መስለው የሚታዩት መሪዎች ያዕቆብና ጴጥሮስ ዮሐንስም እግዚአብሔር በጸጋ ይህን ልዩ የአገልግሎት ዕድል እንደ ሰጠኝ በተረዱ ጊዜ ለእኔና ለበርናባስ የመተባበራቸው ምልክት የሆነውን ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ እነርሱም ወደ አይሁድ እንዲሄዱ ተስማሙ።