ኢዩኤል 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን በሚያዩበት ጊዜ ሕዝቦች ይርበደበዳሉ፤ የሰውም ሁሉ ፊት በፍርሃት ይገረጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤ የሁሉም ፊት ይገረጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቁራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፤ የሰውም ፊት ሁሉ እንደ ድስት ጥላሸት ይጠቍራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቍራል። |
እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ! ወንድ አምጦ ልጅን መውለድ ይችላልን? ታዲያ ወንድ ሁሉ እንደ ወላድ ሴት በእጆቹ ወገቡን ይዞ የማየው ስለምንድን ነው? የእያንዳንዱስ ሰው ፊት ስለምን ገረጣ?
አሁን ግን ፊታቸው እንደ ጥላሸት ስለ ጠቈረ፥ በየመንገዱ ወድቀው ሲገኙ የሚያውቃቸው የለም፤ እንደ እንጨት የደረቀ ቆዳቸው በአጥንታቸው ላይ ተጣብቆአል።
ነነዌ ተደመሰሰች፤ ፈራርሳም ወደመች፤ የሰው ልብ በፍርሃት ቀለጠ፤ ጉልበቶችም ተብረከረኩ፤ የሰው ሁሉ ወገብ ተንቀጠቀጠ። የሰውም ሁሉ ፊት ገረጣ፤
አንበሶች የሚኖሩበትን፥ የአንበሶች ደቦሎች የሚመገቡበትን፥ ወንድና ሴት አንበሶች ከግልገሎቻቸው ጋር ያለ ስጋት የሚዝናኑበትን መስክ ትመስል የነበረችው፥ ያቺ ከተማ አሁን የት አለች?