ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
ኢዮብ 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣ ሞኝን ይገድለዋል፤ ቅናትም ሰውን ያጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂሉን ሰው ብስጭት ይገድለዋል፤ ቂሉንም ቅናት ያጠፋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋልና፥ ቅንዓትም ሰነፉን ያጠፋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋል፥ ሰነፉንም ቅንዓት ያጠፋዋል። |
ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
ኦናን የሚወለዱት ልጆች የእርሱ ያለመሆናቸውን በማወቁ ወደ ወንድሙ ሚስት ሲገባ ዘሩን ወደ ምድር ያፈሰው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በወንድሙ ስም ልጆች እንዳይወለዱ አደረገ።
ሞኞች በልባቸው፦ “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም።
የእስራኤል ሕዝብ እንደ ርግብ የዋህና አእምሮ የጐደላቸው ሆነዋል፤ ስለዚህም ርዳታ ለማግኘት አንድ ጊዜ ወደ ግብጽ ይጣራሉ፤ አንድ ጊዜም ወደ አሦር ይበራሉ።
እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።
እነዚህ ሰዎች በየቤቱ ሾልከው እየገቡ ብዙ ኃጢአት የተከመረባቸውንና በልዩ ልዩ ፍትወት የሚመሩ መንፈሰ ደካማ የሆኑ ሴቶችን እንደሚያጠምዱት ሰዎች ናቸው።