ኢዮብ 4:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሎችህ የሚሰናከሉትን ይደግፉ ነበር፤ የሚብረከረኩትንም ጒልበቶች ታበረታ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጉልበት ታጸና ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቃልህ በሽተኞችን ታስነሣ ነበር፥ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር። |
ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።