ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።
ኢዮብ 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ሸክላ ዕቃ ከዐፈር እንደ ሠራኸኝ አስብ፤ ታዲያ፥ አሁን መልሰህ እንደ ትቢያ ልታደቀኝ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ሸክላ እንዳበጀኸኝ ዐስብ፤ አሁን ደግሞ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጭቃ እንደሠራኸኝ አስታውስ፥ ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጭቃ እንደ ፈጠርኸኝ አስብ፤ ዳግመኛም ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ጭቃ አድርገህ እንደ ለወስኸኝ አስብ፥ ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን? |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።
ከቶ ኃጢአቴን ይቅር አትልልኝምን? የማደርገውንስ በደል አትደመስስልኝምን? ወደ መቃብር መውረጃዬ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ብትፈልገኝ እንኳ አልገኝም።”
ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! እርሱ እኮ ከሸክላ ዕቃዎች እንደ አንዱ ነው፤ አንድ የሸክላ ሥራ ሸክላ ሠሪውን “ምንድን ነው የምታደርገው? እጀታውስ የት አለ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን?
በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ሸክላ ሠሪው ሸክላውን በፈለገው ዐይነት እንደሚሠራው፥ እኔስ በእናንተ ላይ የፈለግኹትን ማድረግ አልችልምን? የሸክላው ጭቃ በሸክላ ሠሪው እጅ እንደሚገኝ እናንተም፥ በእኔ እጅ ናችሁ።
ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።