ኤርምያስ 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰላምና ፈውስ የምናገኝበት ጊዜ ይመጣልናል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፤ በዚህ ፈንታ ሽብር በመምጣቱ ምኞታችን ከንቱ ሆኖ ቀረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ መፈወስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ለይቅርታም ጊዜ መልካም ነገርን አጣን፤ እነሆም ድንጋጤ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ መጠገንን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ። |
እግዚአብሔር ሆይ! ይሁዳን ፈጽመህ ልትጥላት ነውን? የጽዮንንስ ሕዝብ እንደ ጠላህ መቅረትህ ነውን? ለመፈወስ እስከማንችል ድረስ፥ ይህን ያኽል እንድንጐዳ ማድረግህስ ስለምንድን ነው? ሰላም እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፥ ነገር ግን ምንም መልካም ነገር አልገጠመንም፤ ፈውስ እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ሽብር እየበዛ ሄደ።
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።