La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እረኞች ከነመንጋቸው እዚያ ይሰፍራሉ፤ ድንኳኖቻቸውን በከተማይቱ ዙሪያ ይተክላሉ፤ እያንዳንዱም ደስ ባለው ስፍራ መንጋውን ያሰማራል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤ ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤ እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርሷ ይመጣሉ፥ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፥ እያንዳንዱም በስፍራው መንጋውን ያሰማራል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እረ​ኞ​ችና መን​ጎ​ቻ​ቸው ወደ እር​ስዋ ይመ​ጣሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይተ​ክ​ሉ​ባ​ታል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም መን​ጋ​ቸ​ውን ያሰ​ማ​ራሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይመጣሉ፥ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፥ እያንዳንዱም በስፍራው መንጋውን ያሰማራል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 6:3
8 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት።


ብዙ መሪዎች የወይን ተክል ቦታዬን አጥፍተዋል፤ የእርሻ ቦታዎቼንም ረጋግጠዋል፤ ደስ የምታሰኘውን ምድሬንም ወደ በረሓነት ለውጠዋታል።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ ጠባቂዎችህ ተኝተዋል፤ ልዑላንህ አንቀላፍተዋል፤ ሕዝብህ በተራራ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሰበስባቸውም የለም።


ጠላቶችሽ በዙሪያሽ ዐጥር ዐጥረውና ከበው፥ በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ቀን ይመጣል።