“ይህ ቤተ መቅደስ እነሆ አሁን ከፍ ያለ ክብር አለው፤ በዚያን ጊዜ ግን በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚያልፍ ሰው ሁሉ በመገረም ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ስለምን እንደዚህ አደረገ?’ ብሎ ይጠይቃል፤
ኤርምያስ 51:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ከተማ እንዴት ተወረረች! ያቺ የዓለም መመኪያ የነበረችው እርስዋ እንዴት ተያዘች! ባቢሎንስ በሕዝብ ዘንድ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሼሻክ እንዴት ተማረከች! የምድር ሁሉ ትምክሕትስ እንዴት ተያዘች! ባቢሎን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ፣ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሼሻክ እንዴት ተያዘች! ምድርም ሁሉ የሚያመሰግናት እንዴት ተወሰደች! ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መሣቀቅያ እንዴት ሆነች! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የምድርም ሁሉ ክብር እንዴት ተያዘች! እንዴትስ ተወሰደች! ባቢሎን በአሕዛብ መካከል እንዴት ለጥፋት ሆነች! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሼሻክ እንዴት ተያዘች! የምድርም ሁሉ ምስጋና እንዴት ተወሰደች! ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መደነቂያ እንዴት ሆነች! |
“ይህ ቤተ መቅደስ እነሆ አሁን ከፍ ያለ ክብር አለው፤ በዚያን ጊዜ ግን በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚያልፍ ሰው ሁሉ በመገረም ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ስለምን እንደዚህ አደረገ?’ ብሎ ይጠይቃል፤
የባቢሎን መንግሥት ከመንግሥታት ሁሉ እጅግ የተዋበች ናት፤ ለሕዝብዋም መመኪያ ናት፤ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር ባቢሎንን እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ እገለብጣታለሁ!
የዓለምን ሕዝብ እንደ መዶሻ ታደቅ የነበረችው ባቢሎን እርስዋ ራስዋ ደቃለች፤ በዚያች አገር ላይ የደረሰው በሕዝቦች ዘንድ ምንኛ አስደንጋጭ ነው?
ያቺ አገር የፍርስራሽ ክምርና የቀበሮዎች መፈንጫ ትሆናለች፤ ለማየትም የምታሰቅቅ ትሆናለች፤ ማንም አይኖርባትም፤ የሚያያትም ሁሉ ይሳለቅባታል።
“በባሕር ጠረፍ የሚኖሩ ሁሉ አንቺን ከገጠመሽ መጥፎ ዕድል የተነሣ ደንግጠዋል፤ ንጉሦቻቸውም እንኳ ሳይቀሩ ተሸብረዋል፤ በያንዳንዳቸውም ፊት ላይ ፍርሀት ይነበባል።
“ንጉሥ ሆይ! ረጅምና ብርቱ የሆነው ያ ዛፍ አንተ ነህ፤ ታላቅነትህ እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎአል፤ ሥልጣንህም በዓለም ሁሉ ላይ ተንሰራፍቶአል።
ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”