ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”
ኤርምያስ 47:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የሰጠሁትን ሥራ ሳይፈጽም እንዴት ማረፍ ይችላል? እኔ በአስቀሎናና በጠረፎችዋ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዲጥል አዝዤዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣ እንዲወጋ ሲያዝዘው፣ እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣ እንዴት ማረፍ ይችላል?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ትእዛዝ ሰጥቶት እንዴት ዝም ይላል? በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ በዚያ አዘጋጅቶታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በአስቀሎናና በባሕር ዳር በቀሩትም ቦታዎች ላይ ትእዛዝ ሰጥቶአልና፥ በዚያም አዘጋጅቶታልና እንዴት ዝም ትላለህ? በዚያ ትነሣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ትእዛዝ ሰጥቶአልና፥ በዚያም አዘጋጅቶታልና እንዴት ዝም ትላለህ? |
ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”
“ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን ሁሉ የወሰንኩት እኔ ራሴ መሆኔን አልሰማህምን? ዕቅዱን አውጥቼ አሁን ለፍጻሜ ያደረስኩት እኔ ነኝ፤ የተመሸጉ ከተሞችን የፍርስራሽ ክምር እንድታደርጋቸው ኀይልን የሰጠሁህ እኔ ነኝ።
ቸል በማለት የእግዚአብሔርን ሥራ ከልብ የማይፈጽም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር በሚያዘውም ጊዜ ሰይፉን ከደም የሚከለክል የተረገመ ይሁን!
“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፤ እጅህን በቊጣ አማታው፤ ሰይፉም በመደጋገም ተወዛውዞ እየዞረም የሚገድል፥ የሚያሸብርና የሚያርድ ሰይፍ ነው፤
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በፍልስጥኤማውያን ላይ ኀይሌን እጠቀማለሁ፤ ብሪታውያንን እፈጃለሁ፤ በባሕር ጠረፍ የቀሩትንም አጠፋለሁ።
ለጦርነት የሚያዘጋጅ መለከት በከተማ ውስጥ ሲነፋ በፍርሃት የማይንቀጠቀጥ ሕዝብ ይኖራልን? እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይመጣልን?
ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።”