Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 47:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናና በባ​ሕር ዳር በቀ​ሩ​ትም ቦታ​ዎች ላይ ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ በዚ​ያም አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ታ​ልና እን​ዴት ዝም ትላ​ለህ? በዚያ ትነ​ሣ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣ እንዲወጋ ሲያዝዘው፣ እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣ እንዴት ማረፍ ይችላል?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ ትእዛዝ ሰጥቶት እንዴት ዝም ይላል? በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ በዚያ አዘጋጅቶታል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የሰጠሁትን ሥራ ሳይፈጽም እንዴት ማረፍ ይችላል? እኔ በአስቀሎናና በጠረፎችዋ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ አደጋ እንዲጥል አዝዤዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔር በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ትእዛዝ ሰጥቶአልና፥ በዚያም አዘጋጅቶታልና እንዴት ዝም ትላለህ?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 47:7
15 Referencias Cruzadas  

ቍጣ​ዬን በኀ​ጢ​አ​ተኛ ሕዝብ ላይ እል​ካ​ለሁ፤ ይማ​ር​ኳ​ቸ​ውና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ውና እንደ ትቢያ ያደ​ር​ጓ​ቸው ዘንድ ሕዝ​ቤን አዝ​ዛ​ለሁ።


እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም።


“እኔ ጥንት የሠ​ራ​ሁ​ትን አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እኔ በቀ​ድሞ ዘመን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት፥ አሁ​ንም አሕ​ዛ​ብን በም​ሽ​ጎ​ቻ​ቸው፥ በጽኑ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ያጠፉ ዘንድ አዘ​ዝሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።


ወይም በዚ​ያች ምድር ላይ ሰይፍ አም​ጥቼ፦ ሰይፍ ሆይ! በም​ድ​ሪቱ ላይ እለፊ ብል፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም ከእ​ር​ስዋ ባጠፋ፥


ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ እጅ​ህን በእ​ጅህ ላይ አጨ​ብ​ጭብ፤ የተ​ገ​ደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደ​ጋ​ግም፤ ይኸ​ውም የታ​ላቅ ግድያ ሰይፍ ነው፤ ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም።


ወደ ሰገ​ባ​ውም መል​ሰው፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​ባት ስፍራ አት​ደር፤ በተ​ወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ የተ​ሳ​ለች፥ የተ​ሰ​ነ​ገ​ለ​ችም ሁኚ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ መኳ​ን​ን​ቱ​ንም እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ የባ​ሕ​ሩ​ንም ዳር ቅሬታ አጠ​ፋ​ለሁ።


ወይስ በከ​ተማ ውስጥ መለ​ከት ሲነፋ ሕዝቡ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ክፉ ነገር በከ​ተማ ላይ ይመ​ጣ​ልን?


የእግዚአብሔር ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፥ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፥ የመቅሠፍትን በትር፥ እርሱንም ያዘጋጀ ማን እንደ ሆነ ስሙ።


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos