ኤርምያስ 46:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብጽ እንደ ተዋበች ጊደር ናት፤ እርስዋ ከሰሜን በኩል በመጣ ተናካሽ ዝንብ ትወረራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ግብጽ ያማረች ጊደር ናት፤ ነገር ግን ተናዳፊ ዝንብ ከሰሜን ይመጣባታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብጽ እጅግ የተዋበች ጊደር ናት፤ ነገር ግን የቆላ ዝንብ ከሰሜን በኩል ይመጣባታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ግብፅ የተዋበች ጊደር ናት፤ ጥፋት ግን ከሰሜን በኩል ይመጣባታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግብጽ የተዋበች ጊደር ናት፥ ጥፋት ግን ይመጣል፥ ከሰሜን በኩል ይመጣባታል። |
‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ሕዝብ ሆይ! ሕዝቤን፥ በመበዝበዛችሁ ደስታና ሐሴት በማድረግ ፈንጥዛችሁ ነበር፤ በመስክ ላይ እንደምትፈነጭ ጊደር ተቀናጥታችሁ፥ እንደ ሰንጋ ፈረሶችም አሽካክታችሁ ነበር፤
“እስራኤል ማበራየት እንደምትወድ ጊደር ነበረች፤ ነገር ግን በተዋበ ጫንቃዋ ላይ ቀንበር እጭንበታለሁ፤ በዚህ ዐይነት ይሁዳ ያርሳል፤ የያዕቆብ ልጆች በሙሉ ተጠምደው መሬቱን ያለሰልሳሉ፤