ኤርምያስ 4:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በይሁዳ ከተሞች ላይ ጦርነትን እያወጁ ወራሪዎች ከሩቅ አገር በመምጣት ላይ መሆናቸውን ለሕዝቦች አሳውቁ! ለኢየሩሳሌም ሕዝብም ንገሩ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤ ‘ከብበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአሕዛብ አሳውቁ፦ “እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአሕዛብ አሳስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላቶች ከሩቅ ሀገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሕዛብ አሰሙና፦ እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ። |
በዚያም ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።
በስተ ሰሜን የሚኖሩ ሕዝቦች ወደዚህ እንዲመጡ እጠራለሁ፤ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን የይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ይይዙአቸዋል፤ ከዚያም በኢየሩሳሌም መግቢያ በር ላይ ዙፋናቸውን ይዘረጋሉ።
በዚህች ምድር የሚገኙ ሀብታሞችም ድኾችም ሁሉ ይሞታሉ፤ አልቅሶ የሚቀብራቸውም አያገኙም፤ ስለ እነርሱ ሐዘኑን ለመግለጥ ፊቱን የሚነጭም ሆነ ጠጒሩን የሚላጭ አይኖርም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።
ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ አደረገ።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እግዚአብሔር በእናንተ ላይ አደጋ የሚጥል ሕዝብ ከሩቅ ያመጣባችኋል፤ ይህም ሕዝብ ቋንቋውን የማታውቁት፥ ንግግሩንም የማታስተውሉት፥ ጥንታዊነት ያለው ብርቱ ሕዝብ ነው።
ሕዝቡ ብዙ ጊዜ ዐምፀው እግዚአብሔርን ትተዋል፤ ስለዚህ ጠላቶቻቸው እንደ ዱር አንበሶች ወይም እንደ በረሓ ተኲላዎች አደጋ ይጥሉባቸዋል፤ እነዚያም ጠላቶች በከተሞቹ ላይ ሸምቀው ከዚያ የሚወጡትን ሰዎች ሁሉ እንደ ነብር ሆነው ይቦጫጭቁአቸዋል።
“ለአሕዛብ ሁሉ በማወጅ ወሬውን ንገሩ! አርማ አንሥታችሁ ዜናውን አስታውቁ! ከቶ ምሥጢር አድርጋችሁ አታስቀሩ! እነሆ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል የተባለው ጣዖት እንዲያፍር ተደረገ፤ ‘ማርዱክ’ የተባለ ጣዖቷም ተሰባብሮአል፤ የባቢሎን ጣዖቶች አፍረዋል፤ አጸያፊ ምስሎችዋም ተሰባብረዋል።
ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።
ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን አንሥተዋል፤ እነርሱም ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ተቀምጠው የሚጋልቡአቸው ፈረሶች፥ የኮቴአቸው ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ነው። እነሆ እነርሱ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት ተዘጋጅተዋል።”
እስቲ አድምጡ! “እግዚአብሔር ዳግመኛ በጽዮን አይገኝምን? የጽዮን ንጉሥ ዳግመኛ በዚያ አይኖርምን?” እያሉ ሕዝቤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ሲጮኹ እሰማለሁ። ንጉሣቸው እግዚአብሔርም፦ “ጣዖቶቻችሁን በማምለክና ለባዕድ አማልክታችሁም በመስገድ የምታስቈጡኝ ስለምንድን ነው?” ሲል ይመልስላቸዋል፤
እነሆ ቀኝ እጁ ‘ኢየሩሳሌም!’ የሚል ጽሑፍ ያለበትን ፍላጻ አንሥቶ ይይዛል፤ እርሱም ሄዶ ምሽግ ማፍረሻዎችን እንዲያዘጋጅ፥ ለጦርነት የሚያዘጋጅ ድንፋታ እንዲያሰማ፥ ምሽግ ማፍረሻዎችን ወደ ቅጽር በሮቹ እንዲያስጠጋ፥ ዐፈር ቈልሎ እንዲደለድልና የከበባ ምሽግ እንዲሠራ ይነግረዋል።