ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ኤርምያስ 39:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በዚያን ቀን እኔ እግዚአብሔር አንተን አድንሃለሁ፤ ለምትፈራቸው ጠላቶችህ ተላልፈህ አትሰጥም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተን ግን በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ለምትፈራቸው ሰዎች ዐልፈህ አትሰጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምትፈራቸውም ሰዎች እጅ ተላልፈህ አትሰጥም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊታቸውም የተነሣ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።
የማታን ልጅ ሰፋጥያ፥ የፓሽሑር ልጅ ገዳልያ፥ የሼሌምያ ልጅ የሁካልና የመልክያ ልጅ ፓሽሑር እግዚአብሔር የነገረኝን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ማስተማሬን ሰሙ፤
“ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ታላቅ በደል ፈጽመዋል፤ እነሆ ኤርምያስን ጒድጓድ ውስጥ ከተውታል፤ በከተማይቱ ምግብ ስለሌለ እዚያው በረሀብ መሞቱ ነው።”
ስለዚህ ዳንኤል ተይዞ መጥቶ ወደ አንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል ንጉሡ አዘዘ፤ ዳንኤልንም “ሁልጊዜ በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ያድንህ” አለው።
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደረጋችኹት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው!’ ሲል ይመልስላቸዋል።