የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
ኤርምያስ 38:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከዚያ ጒድጓድ ውስጥ በዚያው ገመድ ስበው አወጡኝና በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ዘጉብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በገመዱ ጐትተው ከጕድጓዱ አወጡት። ኤርምያስም በዘበኞች አደባባይ ሰነበተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት፤ ከጉድጓድም አወጡት፤ ኤርምያስም በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት፤ ከጕድጓድም አወጡት፤ ኤርምያስም በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት ከጕድጓድም አወጡት፥ ኤርምያስም በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ። |
የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅጽሩ ማእዘንና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ከሚገኘው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን ክፍል ሁሉ ሠራ። የፓርዖሽ ልጅ ፐዳያ ደግሞ በውሃው ቅጽር በር አጠገብ ወደምሥራቅ የሚያመለክተውን ስፍራና የቤተ መቅደሱን መጠበቂያ ግንብ ይኸውም የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች በሚኖሩበት የከተማይቱ አንድ ክፍል በሆነው “ዖፌል” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ።
ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።
ያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ከበባ ያደረገበት ጊዜ ነበር፤ እኔም በዚያን ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ተዘግቶብኝ ነበር፤
ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ እንዲዘጋብኝ አዘዘ፤ እኔም በዚያ ቈየሁ፤ ዳቦ ከከተማይቱ ጨርሶ እስከ ጠፋም ድረስ ከዳቦ መጋገሪያዎች አንድ ዳቦ በየቀኑ ይሰጠኝ ነበር።
ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።