ነህምያ 3:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25-26 የዑዛይ ልጅ ፓላል ከቅጽሩ ማእዘንና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ከሚገኘው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን ክፍል ሁሉ ሠራ። የፓርዖሽ ልጅ ፐዳያ ደግሞ በውሃው ቅጽር በር አጠገብ ወደምሥራቅ የሚያመለክተውን ስፍራና የቤተ መቅደሱን መጠበቂያ ግንብ ይኸውም የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች በሚኖሩበት የከተማይቱ አንድ ክፍል በሆነው “ዖፌል” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 የኡዛይ ልጅ ፋላል ከቅጥሩ ማእዘን ትይዩና በዘብ መጠበቂያው አደባባይ አጠገብ ካለው ከላይኛው ቤተ መንግሥት መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ ያለውን መልሶ ሠራ። ከርሱም ቀጥሎ የፋሮስ ልጅ ፈዳያና Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 የኡዛይ ልጅ ፓላል በግንቡ መደገፊያ ፊት ለፊት ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 የኡዛይ ልጅ ፋልል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ። ከእርሱም በኋላ የፋሮስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 የኡዛይ ልጅ ፋላል በማዕዘኑ አንጻር ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። Ver Capítulo |
ከምርኮ ከተመለሱት ከእያንዳንዱ ጐሣ ተወጣጥተው የተመዘገቡት የእስራኤል ጐሣዎችና የትውልዳቸው ብዛት ይህ ነው፦ ከፓርዖሽ ወገን የተመዘገቡ 2172 ከሸፋጥያ ወገን የተመዘገቡ 372 ከአራሕ ወገን የተመዘገቡ 652 የኢያሱና የኢዮአብ ትውልድ ጐሣ ከሆነው ከፓሐትሞአብ ወገን የተመዘገቡ 2818 ከዔላም ወገን የተመዘገቡ 1254 ከዛቱ ወገን የተመዘገቡ 845 ከዛካይ ወገን የተመዘገቡ 760 ከቢኑይ ወገን የተመዘገቡ 648 ከቤባይ ወገን የተመዘገቡ 628 ከዓዝጋድ ወገን የተመዘገቡ 2322 ከአዶኒቃም ወገን የተመዘገቡ 667 ከቢግዋይ ወገን የተመዘገቡ 2067 ከዓዲን ወገን የተመዘገቡ 655 ሕዝቅያስ ተብሎ ከሚጠራው ከአጤር ወገን የተመዘገቡ 98 ከሐሹም ወገን የተመዘገቡ 328 ከቤጻይ ወገን የተመዘገቡ 324 ከሐሪፍ ወገን የተመዘገቡ 112 ከገባዖን ወገን የተመዘገቡ 95