እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
ኤርምያስ 36:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ባለ ሥልጣኖቹ ሁሉ ባሮክ ለሕዝቡ ያነበበውን የብራና ጥቅል ይዞ እንዲመጣ ይነግረው ዘንድ ይሁዲን ላኩ፤ (ይሁዲ የነታንያ ልጅ ሲሆን፥ ነታንያ የሸሌምያ ልጅ፥ ሸሌምያም የኩሺ ልጅ ነው፤) ባሮክም የብራናውን ጥቅል ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኳንንቱ ሁሉ የኩሲን ልጅ የሰሌምያን ልጅ የናታንያን ልጅ ይሁዲን፣ “ለሕዝቡ ያነበብኸውን ብራና ይዘህ እንድትመጣ” ብለው ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ብራናውን ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹም ሁሉ፦ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብከውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” የሚል መልእክት በኲሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹም ሁሉ፥ “በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና” ብለው የኩሲ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የናታንያ ልጅ ይሁዳን ወደ ኔርዩ ልጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርዩም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹም ሁሉ፦ በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ። |
እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኰንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ገዳልያን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኰንኖች የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የታንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው የዛንያ ነበሩ፤
“እኔ እግዚአብሔር አንተን ማናገር ከጀመርኩበት ማለትም ኢዮስያስ ከነገሠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስለ እስራኤል፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብና ስለ ሌሎችም ሕዝቦች ሁሉ የነገርኩህን ቃል ሁሉ በብራና ጻፈው፤
ንጉሡም የብራናውን ጥቅል ያመጣለት ዘንድ ይሁዲን አዘዘው፤ እርሱም ብራናውን ከኤሊሻማ ክፍል ወስዶ ለንጉሡና በዙሪያው ቆመው ለነበሩት ባለ ሥልጣኖች ሁሉ አነበበላቸው።
ስለዚህ የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የታንሑሜት ልጅ ሠራያ፥ ከነጦፋ የዔፋይ ልጆች፥ ከማዕካም የዛንያ ከሰዎቻቸው ሁሉ ጋር በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያ መጡ።
ከዚህ በኋላ ዮሐናንና ከእርሱ ጋር ያሉት የሠራዊቱ መሪዎች፥ እስማኤል ገዳልያን ከገደለ በኋላ ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸውን ወታደሮች፥ ሴቶች፥ ሕፃናትና ጃንደረቦች ሁሉ መለሱ።
ሶፎንያስ የኩሺ ልጅ ሲሆን፥ ኩሺ የገዳልያ ልጅ፥ ገዳልያ የአማርያ ልጅ፥ አማርያ ደግሞ የንጉሥ ሕዝቅያስ ልጅ ነው፤ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን እግዚአብሔር ለሰፎንያስ የተናገረው ትንቢት እንደሚከተለው ነው።