ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሔፍጺባ ተብላ የምትጠራ ነበረች፤
ኤርምያስ 32:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቁንም የስሜ መጠሪያ እንዲሆን በተሠራው መቅደሴ አጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በማቆም አርክሰውታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሜ በተጠራበት ቤት አስጸያፊ ጣዖታቸውን አቆሙ፤ አረከሱትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊያረክሱትም ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኵሰታቸውን አኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኵሰታቸውን አኖሩ። |
ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሔፍጺባ ተብላ የምትጠራ ነበረች፤
አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፥ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው።
ምናሴ ባዕዳን አማልክትንና እርሱ ራሱ በዚያ አቁሞት የነበረውን የጣዖት ምስል ከቤተ መቅደስ አወጣ፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱ በቆመበት ኰረብታና በሌሎችም ስፍራዎች ላይ የነበሩትን የጣዖቶች መሠዊያዎች ሁሉ አስወገደ፤ እነዚህንም ሁሉ አንሥቶ፥ ከከተማይቱ ውጪ ጣላቸው፤
በተጨማሪም የካህናት መሪዎችና ሕዝቡ ጣዖቶችን በማምለክ በዙሪያቸው የሚገኙትን ሕዝቦች መጥፎ ምሳሌነት ተከተሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ የቀደሰውን ቤተ መቅደስም አረከሱ፤
ይህንንም የማደርገው ሕዝቡ እኔን ስለ ተዉና ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ይህን ስፍራ ስላረከሱ ነው፤ እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው ከይሁዳ ነገሥታት ጭምር ስለ ነዚህ አማልክት የሚያውቁት ነገር የለም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ንጹሖች ሰዎችን በመግደል ይህ ስፍራ በደም የተሞላ እንዲሆን አድርገውታል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የነቢያቱና የካህናቱ መንፈሳዊ ሕይወት ተበላሽቶአል፤ ሌላው ቀርቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንኳ ክፉ ነገርን ያደርጋሉ፤
ወዳጆቻችሁ ሁሉ ረስተዋችኋል፤ እነርሱ እናንተን አይፈልጉአችሁም፤ ኃጢአታችሁ የበዛ፥ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ ስለ ሆነ፥ እንደ ጠላት መታኋችሁ፤ ያለ ርኅራኄም ቀጣኋችሁ።
እነሆ እናንተም ከጥቂት ቀኖች በፊት ተጸጸታችሁ እኔን ደስ የሚያሰኝ ነገር መሥራት ጀምራችሁ ነበር፤ ሁላችሁም ከእስራኤላውያን ወገን የሆኑ ባሪያዎቻችሁን ነጻ ለመልቀቅ ተስማማችሁ፤ እኔ በምመለክበትም ቤተ መቅደስ ተሰብስባችሁ በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ፤
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት እያቃጠሉ መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሂኖም ሸለቆ ውስጥ ‘ቶፌት’ ተብሎ የሚጠራ መሠዊያ ሠርተዋል፤ ይህም እኔ ያላዘዝኳቸውና በፍጹምም ያላሰብኩት ነገር ነው።