ኤርምያስ 32:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሴዴቅያስ እኔን በዚያ እስረኛ አድርጎ ያስቀመጠኝና የከሰሰኝ እግዚአብሔር የተናገረኝን የትንቢት ቃል ለእርሱ በማሳወቄ ሲሆን፥ እርሱም እንዲህ የሚል ነበር፥ “የባቢሎን ንጉሥ ይህችን ከተማ በኀይል እንዲይዝ ልፈቅድለት ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስም እንዲህ በማለት አሳስሮት ነበር፤ “እንዴት እንደዚህ ያለ ትንቢት ትናገራለህ? ‘እግዚአብሔር፤ “ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም ይይዛታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አሳስሮት ነበርና፦ “ስለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ እርሱም ይይዛታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አስጠብቆት ነበርና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይቺን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ይይዛታል ብለህ ስለምን ትንቢት ትናገራለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አስጠብቆት ነበርና፦ ስለ ምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ እርሱም ይይዛታል፥ |
“ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ።
“የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚፈልጉ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አሳልፌ የምሰጣችሁም በእናንተ ላይ አደጋ የመጣል ተግባሩን ለገታው ለባቢሎናውያን ሠራዊት ነው።
ለንጉሡም እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፦ “እነሆ አንተ የብራናውን ጥቅል አቃጥለሃል፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ መጥቶ ይህችን ምድርና በእርስዋ የሚኖሩትን ሕዝብ፥ እንዲሁም እንስሶችን ሁሉ እንደሚያጠፋ ትንቢት የተናገርከው ስለምንድን ነው?’ ብለህ ኤርምያስን ጠይቀኸዋል፤
እንደገናም አስረዳቸው ዘንድ እግዚአብሔር የነገረኝ ቃል እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኔ ይህችን ከተማ ለባቢሎናውያን ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉአታል።”
ከዚህ በኋላ መኳንንቱ ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፦ “ይህ ሰው ሞት ይገባዋል፤ በእንደዚህ ያለ አነጋገር እየተናገረ በከተማይቱ የቀሩት ወታደሮች ወኔ እንዳይኖራቸው አድርጎአል፤ በከተማይቱ ሰው ሁሉ ላይ የሚያደርገው ይኸው ነው፤ ሕዝቡን ለመጒዳት እንጂ ለመርዳት የሚፈልግ ሰው አይደለም።”
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
እነርሱም “በል እስቲ ንገረን እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይስ እነዚህን እንድታደርግ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።