ኤርምያስ 32:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግዢውንም ውል ምስክሮች ባሉበት ፈርሜ አሸግሁት፤ ገንዘቡንም በሚዛን መዝኜ ሰጠሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውሉም ሰነድ ላይ ፈረምሁ፤ አሸግሁትም። ብሩንም በምስክሮች ፊት በሚዛን መዘንሁለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውሉም ሰነድ ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የውሉንም ወረቀት ጻፍሁ፤ አተምሁትም፤ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። |
በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።
እግዚአብሔር “አሁን ሄደህ ይህ ነገር ለሚመጡት ዘመናት ቋሚ ምስክር ይሆን ዘንድ እነርሱ እያዩ በሰሌዳ ላይ ቅረጸው፤ በመጽሐፍም ጻፈው” አለኝ።
“አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።”
የማሕሴያ የልጅ ልጅ ለሆነው ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት፤ እነዚያን ግልባጮች የሰጠሁት በሐናምኤል፥ የሽያጩን ውል በፈረሙት ምስክሮችና በአደባባዩ ተቀምጠው በነበሩት ሰዎች ፊት ነው፤
ሕዝቡ መሬት ይገዛሉ፤ ውሎች ተፈርመው በምስክሮች ፊት ይታተማሉ፤ ይህም ሁሉ በብንያም ክፍል በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፥ በይሁዳ ገጠር ከተሞች፥ በተራራማው አገር ከተሞች፥ በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ሁሉ ይፈጸማል። ሕዝቡ ሁሉ ወደ ምድራቸው ተመልሰው ንብረታቸውን እንዲረከቡ አደርጋለሁ።”
ስለ ጠዋትና ስለ ማታ መሥዋዕት የተነገረው ራእይ እውነት ነው፤ አንተ ግን ይህ ራእይ የሚፈጸምበት ጊዜ ሩቅ ስለ ሆነ በምሥጢር ያዘው” አለኝ።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
የእርሱ ለመሆናችን ማስረጃ የሚሆን ማኅተሙን በእኛ ላይ ያደረገና ወደ ፊት ለእኛ ስለሚሰጠን ሀብት በልባችን መንፈስ ቅዱስን እንደ ዋስትና አድርጎ የሰጠን እርሱ ነው።
እናንተም የመዳናችሁ መልካም ዜና የሆነውን የእውነት ቃል በሰማችሁ ጊዜ በክርስቶስ አምናችኋል፤ እንዲሁም እርሱ ሊሰጣችሁ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታትማችኋል።
ሰዎቹም በአገሪቱ በመላ ተዘዋወሩ፤ ከተሞቹንም ሁሉ መዝግበው ምድሪቱ ለሰባት ነገድ እንዴት እንደምትከፈል በጽሑፍ ገለጡ፤ ከዚህም በኋላ ኢያሱ ወዳለበት ወደ ሴሎ ተመልሰው መጡ፤
የሕያው አምላክን ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክም ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ ምድርንና ባሕርን እንዲጐዱ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት ድምፁን ከፍ አድርጎ፥
የምድርን ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው፤ መጒዳት ያለባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማኅተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነበር።
ቦዔዝ በከተማው በር አጠገብ ወደሚገኘው መሰብሰቢያ አደባባይ ሄዶ ተቀመጠ፤ ከዚህ በፊት ቦዔዝ ስለ እርሱ የተናገረው የአቤሜሌክ የቅርብ ዘመድ ወደዚያው ቦታ መጣ፤ ቦዔዝም በስሙ ጠርቶ “ወንድሜ ሆይ! ወደዚህ መጥተህ አጠገቤ ተቀመጥ” አለው። እርሱም ወደዚያ ሄዶ ተቀመጠ።