La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 29:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ደብዳቤውንም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላካቸው በሻፋን ልጅ በኤልዓሳና በሕልቂያ ልጅ በገማርያ እጅ ላክሁት፤ የደብዳቤውም ፍሬ ነገር እንዲህ የሚል ነው፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደብዳቤውንም ከይሁዳ ንጉሥ ከሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር በተላኩት መልእክተኞች በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ላከው፤ ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን ላከው፤ እንዲህም የሚል ነበር፦

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤር​ም​ያ​ስም የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን በላ​ካ​ቸው በሳ​ፋን ልጅ በኤ​ል​ዓ​ሣና በኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ በገ​ማ​ርያ እጅ ደብ​ዳ​ቤ​ውን እን​ዲህ ሲል ላከው፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው፦

Ver Capítulo



ኤርምያስ 29:3
11 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኀላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤


ወዲያውኑ ለካህኑ ለሒልቂያ፥ የሳፋን ልጅ ለሆነው ለአሒቃም፥ የሚካያ ልጅ ለሆነው ለዐክቦር፥ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ለሆነው ለሳፋንና የንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለሆነው ለዓሳያ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፤


ከዚህ በኋላ ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለሒልቂያ ሰጠ፤ ሒልቂያም “የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ” ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፤


ሔሌጽ፥ ኤልዓሳ፥


ሻሉም ሒልቂያን ወለደ፤ ሒልቂያ ዐዛርያስን ወለደ፤


ከዚህም በኋላ ንጉሡ ለሒልቂያ፥ ለሳፋን ልጅ ለአሒቃም፥ ለሚክያስ ልጅ ለዐብዶን፥ ለቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ለሳፋንና የንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለሆነው ለዓሳያ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፥


ይሁን እንጂ ንጉሥ ኢዮአቄም የዓክቦር ልጅ ኤልናታንና ሌሎችም ሰዎች ወደ ግብጽ ወርደው ኡሪያን ይዘው እንዲመጡ አዘዘ፤


እኔ ግን የሳፋን ልጅ አሒቃም ይከላከልልኝ ስለ ነበር ይገድሉኝ ዘንድ ለሕዝቡ ተላልፌ አልተሰጠሁም።


ኤልናታን፥ ደላያና ገማርያ ንጉሡ የብራናውን ጥቅል እንዳያቃጥል ቢለምኑትም እንኳ ሊያዳምጣቸው አልፈለገም።


ታስሬበት ከነበረው በቤተ መንግሥቱ ግቢ ከሚገኘው ዘብ ጠባቂዎች ክፍል እንድወጣ አስደረገ፤ እኔም የሳፋን የልጅ ልጅ በሆነው በአሒቃም ልጅ በገዳልያ እጅ ወደ ቤቴ ተወሰድኩ፤ እኔም ከሕዝቤ ጋር በዚያ ኖርኩ።


የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤