ኤርምያስ 27:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስም ይህንኑ ቃል እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ለባቢሎን ንጉሥ ብትገብር፥ እርሱንና ሕዝቡንም ብታገለግል በሕይወት መኖር ትችላለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህንኑ መልእክት እንዲህ ብዬ ነገርሁት፤ “ዐንገታችሁን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዝቅ አድርጉ፤ እርሱንና ሕዝቡን አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በእነዚህ ቃላት ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ ለእርሱና ለሕዝቡም አገልግሉአቸው በሕይወትም ኑሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህን ቃል ሁሉ ተናገርሁ፥ “ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ለእርሱና ለሕዝቡም ተገዙላቸው በሕይወትም ኑሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በዚህ ቃል ተናገርሁ፦ ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ ለእርሱና ለሕዝቡም ተገዙላቸው በሕይወትም ኑሩ። |
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
በዚህች ከተማ የሚቀሩ ሁሉ በጦርነት ወይም በራብ፥ ወይም በወረርሽኝ ይሞታሉ፤ አሁን ከተማይቱን ከበው ወዳሉት ወደ ባቢሎናውያን ሄዶ እጁን የሚሰጥ ግን አይሞትም፤ ሌላው ቢቀር ሕይወቱን ያተርፋል፤
“ነገር ግን ማንኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እርሱን አላገለግልም፤ በቀንበሩም ሥር ሆኜ አልገዛም’ ቢል ናቡከደነፆር ራሱ እንዲደመስሰው እስከ ፈቀድኩለት ድረስ፥ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲቀጡ አደርጋለሁ።
በዚሁ ዘመን፥ ማለትም ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር የገባዖን ሰው የሆነው የዐዙር ልጅ ሐናንያ በቤተ መቅደስ ተናገረኝ፤ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦
ከዚህም በኋላ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ያለውን ሁሉ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “የባቢሎን ንጉሥ ለላካቸው ባለ ሥልጣኖች እጅህን ብትሰጥ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ ከመቃጠል ትድናለች፤ አንተና ቤተሰብህም ሁሉ ከጥፋት ትድናላችሁ፤