ኤርምያስ 26:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ወደ ንጉሥ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ፤ ንጉሡም ኡሪያ እንዲገደልና በሕዝብ መቃብር ስፍራ እንዲጣል አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ኦርዮን ከግብጽ አምጥተው፣ ወደ ንጉሥ ኢዮአቄም ወሰዱት፤ እርሱም በሰይፍ ገደለው፤ ሬሳውንም ተራ ሰዎች በሚቀበሩበት ስፍራ ጣለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦርዮንንም ከግብጽ አውጥተው ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ፤ እርሱም በሰይፍ ገደለው ሬሳውንም ክቡራን ባልሆኑ ሰዎች መቃብር ጣለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅም ኡርያን አውጥተው ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ፤ እርሱም በሰይፍ ገደለው፤ ሬሳውንም በሕዝብ መቃብር ጣለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብጽም ኦርዮን አውጥተው ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ፥ እርሱም በሰይፍ ገደለው ሬሳውንም ክቡራን ባልሆኑ ሰዎች መቃብር ጣለው። |
ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።”
ንጉሥ ኢዮአቄም ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ይህ ነው፦ ‘ከዘርህ በዳዊት መንግሥት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከቶ አይኖርም፤ ሬሳህም የትም ተጥሎ ለቀን ፀሐይ ሐሩርና ለሌሊት ቊር የተጋለጠ ይሆናል፤
አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን የገደሉ እኛንም አሳደው ከአገር ያስወጡ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑና ሰዎችን ሁሉ የሚጠሉ ናቸው፤